መዝሙር 187 የሱስ ሆይ ተቀበለኝ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ የሱስ ሆይ ተቀበለኝ
እኔ ወደ አንተ ስመጣ።
በመንፈስህ ጠብቀኝ
ከመለየት ከአንተ ጌታ
በየዕለት በየሰዓት
በደምህ እኔን አንጻኝ።
በምሕረትህ አቅርበኝ
በታላቅ ፍቅርህ ውስጥ ሰውረኝ።
፪፡ በዚህ ዓለም እስካለሁ
የሱስ ሆይ ምራኝ ባካሄዴ።
ባንተ ከተመራሁኝ
አይሳሳተኝም መንገዴ።
በየዕለት . . .።
፫፡ ፍቅሬ እንዲጸናልኝ
በቅዱስ ቃልህ እኔን ምራኝ።
እሰማይ ስታደርሰኝ
እንዳመሰግንህ አምላኬ።
በየዕለት . . .።
