Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 186 ስማልኝ ጸሎቴን ጌታ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 186 ስማልኝ ጸሎቴን ጌታ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ስማልኝ ጸሎቴን ጌታ
ምራኝ ወደሚያነፃኝ ምንጭ፥
በኃጢአቴም እንዳልሞት፥
ወደ አንተ እመጣለሁ።
ወደ አንተ እመጣለሁ፥
ወደ አንተ እመጣለሁ፥
ዕዳዬን ሁሉ ከፍለሃል፥
ወደ አንተ እመጣለሁ።
፪፡ በክቡር ደምህ ተዋጀሁ
ተስፋዬም ሁሉ በአንተ ነው።
ምኞቴን ተመልከት ጌታ፥
ወዳንተ እመጣለሁ።
ወደ አንተ . . .።
፫፡ በደምህ ልቤን አንፃልኝ
ኃጢአቴን ደምስስልኝ።
የልቤንም ፈቃድ ቀድስ፥
ወደ አንተ እመጣለሁ።
ወደ አንተ . . .።

Exit mobile version