Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 180 ሁሉን በሚችል የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 180 ሁሉን በሚችል የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ሁሉን በሚችል በእግዚአብሔር አብ አምናለሁ
የሰማይ የምድር ፈጣሪ።
ደግሞ በአንድ ልጁ በየሱስ ክርስቶስ፥
ከሰማያት በወረደው፥
በመንፈስ ቅዱስ በተፀነሰው፥
ከድንግል ማርያም በተወለደው፥
በጲላጦስ በጴንጤናዊው ዘመን፥
መከራ በተቀበለው።
፪፡ በመስቀል በውርደት በተሰቀለው
በሞተ በተቀበረው።
ወደ ሲኦል ወርዶ፥ በሦስተኛው ቀን
ከሞት በኃይል በተነሣው፥
ሁሉን በሚችል በአብ ቀኝ ባለው፥
የጌቶች ጌታ የነገሥታት ንጉሥ፥
በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ
በሚመለሰው አምናለሁ።
፫፡ ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ ባንዲት ቅድስት
የሐዋርያት ቤተክርስቲያን፥
በኃጢአት ማስተሰሪያ ባንዲት ጥምቀት፥
በቅዱሳንም አንድነት፥
በኃጢአት ስርየት በሙታን ትንሣኤ፥
በዘለዓለም ሕይወት አምናለሁ።
አምናለሁ በዚህ እውነተኛ እምነት
እንዳላሳዝንህ እርዳኝ።

Exit mobile version