Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 176 ከመንፈስ ቅዱስ ከውኃ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 176 ከመንፈስ ቅዱስ ከውኃ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ከመንፈስ ቅዱስ ከውኃ
ካልተወለድህ ዳግም
የአምላክህን መንግሥት ገብተህ
ልታይ አትችልም።
፪፡ ለአንተ እንሰግዳለን
በትሕትና መንፈስ
ስትጠመቅ ገብተህ አንተ
በማየ ዮርዳኖስ።
፫፡ ልትጠመቅ አንተ ስትሔድ
በዮሐንስ እጅ
እርሱም አለ ካንተ ልጠመቅ
እኔ እሻለሁ እንጂ።
፬፡ አንተ አጥምቀኝ አለው ጌታም
ጽድቅን ለመፈጸም
ለሕዝብም እንዲሆን ሕይወት
እሰከ ዘለዓለም።
፭፡ ጌታ ሲጠመቅ በውኃ
ከድንግል ተወልዶ
በነጭ ርግብ አምሳል ታየ
መንፈስ ቅዱስ ወርዶ።
፮፡ በዮሐንስ እጅ ተጠምቆ
ከውኃው ሲወጣ
እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ
በደመና መጣ።
፯፡ ይህ ነው እኔ የሰደድሁት
የምወደው ልጄ
በደሙ ዓለምን ሊያድን
እንዲሞት ወድጄ።

Exit mobile version