መዝሙር 174 ሁሉም ሩጠው አክሊል አንዱ ያገኛል የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ሁሉም ሩጠው አክሊል አንዱ ያገኛል
ወንድሜ እንድታገኘው ጣር።
ቀድመው የገቡት ወዳምላክ ፀዳል
ነፃ ሆነዋል ከምድር ዳር።
ስትሮጥም ዓይንህ አይገላመጥ
የከንቱነት ደስታ አትመኝ።
ቅዱስ አክሊሉንም እንድታገኝ
መንፈስ ቅዱስ የሚለውን አድምጥ።
፪፡ የማይጠፋውን አክሊል ለማግኘት
የሚመኝ በጣም ይጋደላል።
አንተም ለዘለዓለም ደኅንነት
ዓለምን መካድ ይገባሃል።
የዚህ ዓለም ጥሪት ምን ይረባል?
እንደ ጢስ ይጠፋል ደስታው።
የሱስ የሚሰጠው ግን ይኖራል፡
በርሱ የሚያምን ብፁዕ ነው።
፫፡ የሱስ ላንተ መስቀል ሲሸከም
አክሊሉን አዘጋጅቶልሃል።
በርሱ የሾህ ዘውድ ስለ ተጫነም
የብፅዕና ዘውድ ይቆይሃል።
የሰማይን ርስት እንድትወርሰው
እንድታገኝ ቅዱስ አክሊሉን
በመድኃኒታችን ደም በማመን
እስከ ሞት ድረስ የጸናህ ሁን።
