መዝሙር 166 በሰማይ ያለ አባታችን የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ በሰማይ ያለህ አባታችን
ክቡር ስምህ ይቀደስ
መንግሥትህ ትምጣልን አሁን
ትውረድ ወደ ምድራችን።
፪፡ በምድር ይሁን ፈቃድህ
በሰማይ እንደሆነ፥
የዕለት እንጀራችንን፥
ስጠን አምላካችን ሆይ።
፫፡ በደላችንን ይቅር በለን
ፊትህ ተንበርክከናል፥
እኛ ይቅር እንደምንል፥
አንተም እኛን ይቅር በል።
፬፡ አባት ሆይ ወደ ፈተና
ልጆችህን አታስገባን፥
ታደገን አምላካችን ሆይ፥
ከክፉውም አድነን።
፭፡ መንግሥት ያንተ እንደሆነ
ሥልጣን ክብርም ያንተ ነው፥
ፍርድ ቸርነት ምሕረትም፥
ያንተ ነው ለዘላለም።
አሜን።