Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 159 አባታችን ጌታቸን ሆይ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 159 አባታችን ጌታቸን ሆይ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ አባታችን ጌታቸን ሆይ
የምትኖር በሰማይ
መንግሥትህ ትምጣልን ከላይ
ክብርህን እንድናይ
ክብርህን እንድናይ።
፪፡ ፈቃድህ በሰማይ ቀድሞ
ጸንቶ እንደ ኖረ
እንዲሁም በምድር ደግሞ
ይሁን ዕለት ዕለት
ይሁን ዕለት ዕለት።
፫፡ ስጠነ ለሕዝብህ ዛሬ
የዕለት ሲሳያችን
በደላችንንም ሁሉ
ይቅር እንድትለን
ይቅር እንድትለን።
፬፡ ጌታ ሆይ አታግባን አሁን
ከክፉ ፈተና
አምላክ አንተ ካልረዳኸን
ኃይል የለንምና
ኃይል የለንምና።
፭፡ ኃይልና ምስጋና ክብርም
መንግሥትም ያንተ ናት
አሜን እስከ ዘለዓለም
ይሁንልን ዕረፍት
ይሁንልን ዕረፍት።

Exit mobile version