መዝሙር 155 ወደ እግዜአብሔር ቤት የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
ወደ እግዜአብሔር ቤት እንሂድ
ሲሉኝ ደስ አለኝ
ቃሉን እንስማ እንሂድ ሲሉኝ
ደስ አለኝ
ና ና እንጸልይ እንሂድ ሲሉኝ
ደስ አለኝ
ና ና እንዘምር እንሂድ ሲሉኝ
ደስ አለኝ፤
ደስ አለኝ።
፩፡ ይባርከኛል አውቃለሁ
ያስተምረኛል አምናለሁ
ሕይወቴን ለርሱ እሰጣለሁ።
ወደ እግዚአብሔር ቤት . . .።
፪፡ ቃሉን ቢሰጠኝ እበላለሁ
መንፈሱን ቢያፈስ እጠጣለሁ
እንዲለውጠኝ እሻለሁ።
ወደ እግዚአብሔር ቤት . . .።
፫፡ ሸክሜን ሁሉ አወርዳለሁ
ኃጢአቴን እናዘዛለሁ
በእውነት ታድሼ እሄዳለሁ።
ወደ እግዚአብሔር ቤት . . .።
