መዝሙር 153 ስማነ ጌታ ሆይ አሁን የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ስማነ ጌታ ሆይ አሁን
ለክብርህ ስንዘምር
በዚህ በእንግድነት አገር
ጠፍተን እንዳንቀር
፪፡ አቤቱ መሥርታት ዛሬ
ወንጌል መቅደስህን።
በጥልቁ ባሕር ዳር ቁመን
እንዳናይ መፍረስዋን።
፫፡ ጌታ ሆይ ላክልን ፈጥነህ
ቅዱስ መንፈስህን፤
ለማየት ናፍቀናል ሕዝብህ
ገነት መኖርያህን።
፬፡ ጌታ ሆይ አንተ ጠብቀን
ከመከራና ሞት፤
ይገለጥ በኛ ላይ አሁን
የምሕረትህ ብዛት።
፭፡ ልቅሷችንን ተቀበለን
ፈተና ስንገባ፤
አይተህ ዝም አትልምና
የድሆችን ዕንባ።
