Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 152 ጸጋህ ሲወርድ እንደዝናብ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 152 ጸጋህ ሲወርድ እንደዝናብ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ጸጋህ ሲወርድ እንደ ዝናብ
የነቢያት ቃል ሲፈጸም
የደስታ ዘመን እንዲሆን
ለምድር ሁሉ ሰላም።
ጌታ ከአርያም
መንፈስህን ላክልን።
በረከትን አዝንብልን
ጸጋህን አሁን ስጠን።
፪፡ ጸጋህ ሲወርድ እንደዝናብ
እንዲሞላ ልባችን
መስክ ውኃ እንደሚቀበል
ነፍሳችንን አርካልን
ጌታ ከአርያም . . .።
፫፡ ጌታ ሆይ ጸጋህን ስጠን
በረከት አውርድልን
ዛሬ ሁሉን ፈጽምልን
ስማ ጸሎታችንን።
ጌታ ከአርያም . . .።

Exit mobile version