Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 149 የጸሎት ሰዓት የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 149 የጸሎት ሰዓት የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ የጸሎት ሰዓት
የደስታ ሰዓት
አምላኬን የምቀርብበት፥
የሱስንም የምሻበት፥
ምኞቴን የምነግርበት።
ከመከራ እድናለሁ፥
ብርታትንም አገኛለሁ፥
ከፈተና አመልጣለሁ
በጸሎቴ ጊዜ ሁሉ።
፪፡ የጸሎት ሰዓት
የደስታ ሰዓት
በእምነት ይምጠጋበት፥
ጌታን የምወድስበት፥
ነፍሴ የምትረካበት።
ወደ ዙፋኑ ሲጠራኝ፥
በጸጋው ደኅንነት አለኝ።
መከራዬን እረሳለሁ
በእርሱም እማጸናለሁ።
፫፡ የጸሎት ሰዓት
የደስታ ሰዓት
ዕረፍትን የማገኝበት፥
ከኀዘን የምጽናናበት፥
እስክደርስ ወደ ሰማይ ቤት።
በትንሣኤ እነሣለሁ፥
ወደ ጌታ እቀርባለሁ፥
ዋጋዬን እቀበላለሁ፥
በዕልልታ እዘምራለሁ።

Exit mobile version