መዝሙር 148 ና ቸር መሐሪ አንተ ነህ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ና ቸር መሐሪ አንተ ነህ
የበጎችህ እረኛ
አሳየን ቅዱስ ቁስልህን
የቆሰልኸውን ስለኛ።
በደብረ ጽዮን ሰብስበን
በዚያ ነው ደስ የሚለን
በዚያ ካንተ ጋራ።
፪፡ የሱስ ሆይ በልባችን ላይ
የፍቅርህን ጐርፍ አፍስስ
የእምነት ጉድለትን ጭንቀት
የደምህ ኃይል ይፈውስ።
አንተ ታላቅ ይቅር ባይ ሆይ
ና ለውጥ በፍቅርህ ፀሐይ
ብርዳችንን በሙቀት።