መዝሙር 147 ባንተ ደስ ይለኛል የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ባንተ ደስ ይለኛል የኔ ጌታ
ልጽና በመንፈስህ እንዳልረታ
አርቄ እያየሁ ጽድቅ አክሊሌን
በተስፋ እንድጓዝ እርዳኝ ልጅህን።
የርስቴ መያዣ መንፈስህ
ያጽናናኝ ሁልጊዜ እንዳልረሳህ።
የርስቴ መያዣ መንፈስህ
ያጽናናኝ ሁልጊዜ እንዳልረሳህ።
፪፡ የማትሰለቸኝ የማትረሳኝ
ረዳት ለጉዞዬ ለነፍሴ አጽናኝ
ዓይኔን እንዳላነሳው ከመስቀልህ
ሐሳቤን ጠቅልለው ወደ ሞትህ።
ዓይኔን እንዳላነሳው ከመስቀልህ
ሐሳቤን ጠቅልለው ወደ ሞትህ።
፫፡ ዝናህ የገነነው በዓለም ላይ
መቼ ትመጣለህ ፊትህን እንዳይ።
በጣም ጓጉቻለሁ የኔ ጌታ።
የሱሴ እንዳይህ ማራናታ።
በጣም ጓጉቻለሁ የኔ ጌታ።
የሱሴ እንዳይህ ማራናታ።
