መዝሙር 145 የጌታ መለከት ሲነፋ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ የጌታ መለከት ሲነፋ
ጊዜውም ሲፈጸም፥
ክርስቶስ በክብር ይገለጣል ዳግም።
በርሱ ያመኑ ሁሉ ከፊቱ ሲሰበሰቡ፥
ስሜ ሲጠራ እገኛለሁ እዚያ።
ስሜ በተጠራ ጊዜ፥
ስሜ በተጠራ ጊዜ፥
ስሜ በተጠራ ጊዜ፥
ስሜ ሲጠራ፥ እገኛለሁ እዚያ።
፪፡ በዚያ ብሩህ ቀን
በጌታ የሞቱት ሲነሱ፥
ይላቸዋል ብሩካን ወደኔ ኑ።
አእላፋት መላእክትም ይከቡታል በዙሪያው።
ስሜ ሲጠራ እገኛለሁ እዚያ።
ስሜ በተጠራ ጊዜ . . .።
፫፡ መንጋህ ነን ጠብቀን
ጠላታችን እንዳያጠፋን፥
እየንም እንደ ክብር ዓይንህ ብሌን።
ጌታ ጠርተህ ቀስቅሰን
ቁመን እንድንገኝ እዚያ።
ስሜ ሲጠራ እገኛለሁ እዚያ።
ስሜ በተጠራ ጊዜ . . .።
