መዝሙር 144 እንዴት ያለ የድል ቀን የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ እንዴት ያለ የድል ቀን፥ የድል ቀን፥
የድል ቀን፥
እንዴት ያለ የድል ቀን ይሆናል።
ከጭንቀት የማርፍበት፥
አምላኬን የማይበት፥
እንዴት ያለ የድል ቀን ይሆናል።
፪፡ እንዴት ያለ ግሩም ቀን፥ ግሩም ቀን፥
ግሩም ቀን
እንዴት ያለ ግሩም ቀን ይሆናል።
የሱስ ባለም ሲያበራ፥
ልጆቹንም ሲጠራ፥
እንዴት ያለ ግሩም ቀን ይሆናል።
፫፡ እንዴት ያለ ድንቅ ቀን፥ ድንቅ ቀን፥
ድንቅ ቀን
እንዴት ያለ የድል ቀን ይሆናል።
ባየር ጌታችን መጥቶ፥
ሲነጥቀን እኛን ጠርቶ፥
እንዴት ያለ ድንቅ ቀን ይሆናል።
፬፡ እንዴት ያለ ታላቅ ቀን፥ ታላቅ ቀን፥
ታላቅ ቀን
እንዴት ያለ ታላቅ ቀን ይሆናል።
ልጆቹ ሲነጠቁ፥
የቀሩት ሲጨነቁ፥
እንዴ ያለ ታላቅ ቀን ይሆናል።
፭፡ እንዴት ያለ የድል ቀን፥ የድል ቀን፥
የድል ቀን
እንዴት ያለ የድል ቀን ይሆናል።
ነጭ ልብሳችንን ለብሰን፥
ዘንባባ ቅጠል ይዘን፥
እንዴት ያለ የድል ቀን ይሆናል።
፮፡ እንዴት ያለ ታላቅ ቀን፥ ታላቅ ቀን፥
ታላቅ ቀን
እንዴት ያለ ታላቅ ቀን ይሆናል።
ሆሳዕና ስንዘምር፥
በሰማያዊ አገር፥
የእንዴት ያለ ታላቅ ቀን ይሆናል።
፯፡ እንዴት ያለ የድል ቀን፥ የድል ቀን፥
የድል ቀን
አንዴት ያለ የድል ቀን ይሆናል።
ለበጉ ለአምላካችን፥
ስንዘምር ሁላችን፥
እንዴት ያለ የድል ቀን ይሆናል።
