መዝሙር 141 መለከት ንፉ በታላቅ ድምፅ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ መለከት ንፉ በታላቅ ድምፅ
የሱስ ይመለሳል፤
ደስ ይበላችሁ ዘምሩም፥
የሱስ ይመለሳል።
ይመለሳል ይመለሳል
የሱስ ይመለሳል።
፪፡ ተራሮች ጩሁ ሜዳም አብሮ
የሱስ ይመለሳል፤
ይገለጣል የታረደው በግ፥
የሱስ ይመለሳል።
ይመለሳል . . .።
፫፡ አውጅ ባሕር በታላቅ ቃል
የሱስ ይመለሳል፤
ይገለጣል የታረደው በግ፥
የሱስ ይመለሳል።
ይመለሳል . . .።
፬፡ ምድር ሲናወጥ ይታወቃል
የሱስ ይመለሳል፤
ዓውሎ ነፋስ ይነግረናል፥
የሱስ ይመለሳል።
ይመለሳል . . .።
፭፡ በሕዝብ መቆጣት ይታወቃል
የሱስ ይመለሳል፤
ሕዝብ ይራወጣል እውቀት ይበዛል፥
የሱስ ይመለሳል።
ይመለሳል . . .።
