Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 137 አልመለከትም ያለፈ ሕይወቴን የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 137 አልመለከትም ያለፈ ሕይወቴን የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ አልመለከትም ያለፈ ሕይወቴን
በከንቱ እንደ ባከንሁ ጌታ ያውቃል።
ንስሐ ገብቼ ሁሉን ልናዘዝ
ይቅር ብሎ ለሚደመስሰው።
፪፡ አልመለከትም ወደፊት ዕቅዴን
ቢያጥር ቢረዝም ዘመኔ የርሱ ነው።
ፈተናዬን እርሱ ይቋቋመዋል
የኃጢአቴን ሸክም ያነሣዋል።
፫፡ አልመለከተም ዙሪያዬ ያለውን
ሁከቱ ሞገዱ ያስፈራራኛል።
ዓለም በክፋት ይተበትበኛል፥
ከንቱ ተስፋውም ሰላም ይነሣኛል።
፬፡ አልመለከተም የራሴን ትምክህት
የምመካበት አንዳች የለኝም።
ከንቱነቴና ጉድለቴ ይልቃል
ደካማ ጥረቴም አይረባኝም።
፭፡ እመለከታለሁ ወደ ጌታዬ
ኢየሱስን ሳይ እበረታለሁ።
የልቤ ፍርሃት ጭንቀቴም ጸጥ ይላል
ደስታ ሰላም ተስፋውም ያረካኛል።

Exit mobile version