Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 135 አምላኬ ፊትህን አትሰውርብኝ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 135 አምላኬ ፊትህን አትሰውርብኝ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ አምላኬ ፊትህን አትሰውርብኝ
ድምፄን ስማኝ ቅረብ አጽናናኝ።
አንተ የታመንክ የነፍሴ
መድኃኒቴ ሆይ
አትመጣም ወይ?
አትመጣም ወይ?
፪፡ በዚህ በምድር እንግዳ ነኝና
ገና አላየሁም ያንተን ብፅዕና።
አንተ የታመክ . . .።
፫፡ በዚህ በእንግድነት አገር ሳለሁ
ወደ ሰማይህ በናፍቆት አያለሁ።
አንተ የታመንክ . . .።
፬፡ እስክትመጣም በልቤ ውስጥ ንገሥ
ኀዘኔን አቅልለህ ደስታዬን ቀድስ።
አንተ የታመንክ . . .።
፭፡ አንተኑ ብቻ አቤቱ እንድፈራ
ልቤ በመንፈስ ዘወትር ይመራ።
አንተ የታመንከ . . .።
፮፡ የምትሰጠኝ ዘውድ እንዳይቀርብኝ
አምላኬ እምነት ጨምርልኝ።
አንተ የታመንክ . . .።

Exit mobile version