Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 133 አምላኬ ወዳንተ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 133 አምላኬ ወዳንተ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ አምላኬ ወዳንተ
እቀርባለሁ
ከከባድ ሸክሜ
ዕረፍት እንዳገኝ
መዝሙሬን ስዘምር።
አምላኬ ወዳንተ
አምላኬ ወዳንተ
እቀርባለሁ።
፪፡ ደካማ ምእመን ነኝ
በዓለም ላይ
ፀሐዬ ጨለማ
ዕረፍቴም ስቃይ
ቢሆንብኝ እንኳ።
አምላኬ . . .።
፫፡ የሰማይን መንገድ
ግለጥልኝ፤
በታላቅ ምሕረትህ
ወደ ላይ ምራኝ
ድምጽህን ሰምቼ።
አምላኬ . . .።
፬፡ በነቃ ሐሳቤ
ላመስግንህ፤
በኅዘኔ ሥፍራ
አንተን ልቅረብህ
ጸሎቴን ለማድረስ።
አምላኬ . . .።
፭፡ ከዓለም በደስታ
ወደ ሰማይ፤
ልሄድ በእልልታ
እመኛለሁ
መዝሙሬን ስዘምር።
አምላኬ . . .።

Exit mobile version