መዝሙር 132 ከየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ በቀር የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ከየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ በቀር
የምድንበት የለኝም።
ግን በርሱ አምኜ ልድፈር
የአምላክ ሕግ ሲከሰኝም።
ለማመን ቢያስቸግርም
የየሱስ ቃል አይፋለስም።
ለማመን ቢያስቸግርም
የየሱስ ቃል አይፋለስም።
፪፡ ሕይወት ሊሰጠኝ የሚችል
የኃጢአት ይቅርታ ነው
እኔን ከፍርድ የሚያስጥል
ሙሉ ይቅርታ ብቻ ነው።
ይቅርታ ባይኖርልኝ ግን
ተስፋና ሕይወት የለኝም።
ይቅርታ ባይኖርልኝ ግን
ተስፋና ሕይወት የለኝም።
፫፡ የምመካበት ጋሻዬ
የኃጢአት ይቅርታ ነው።
በጭንቀት ሁሉ ደስታዬ
የኃጢአት ይቅርታ ነው።
በየሱስ ደም ስርየት ሳገኝ
እስከ ዘላለም ብፁዕ ነኝ።
በየሱስ ደም ስርየት ሳገኝ
እስከ ዘላለም ብፁዕ ነኝ።
፬፡ ቸር የሱስ ሆይ ይቅርታህን
በጸጋህ ሁሉ ቀን ስጠኝ።
በልቤም ውስጥ ሰላምህን
ይቅርታህ ሁልጊዜ ይስጠኝ።
በደምህ አምባ ውስጥ ስኖር
አልፈራም የጠላቴን ጦር።
በደምህ አምባ ውስጥ ስኖር
አልፈራም የጠላቴን ጦር።