መዝሙር 131 መጣሁ ወደ መስቀልህ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ መጣሁ ወደ መስቀልህ
ምስኪን ነኝ ደካማም ነኝ
ወዳንተ እንድቀርብህ
መድኃኒቴ ሆይ እርዳኝ።
ባንተ አምናለሁ
ብሩክ የቀራንዮ በግ
ተንበርክኬ በጸሎት
አድነኝ የሱስ አድነኝ
፪፡ ያለኝን ሀብት በሙሉ
ሥጋዬን ቢሆን ነፍሴን
ለአንተ እሰጣለሁ
ለዘላለም ያንተ ነው።
ባንተ . . .።
፫፡ ያንተን ተስፋ አምናለሁ
እርዳኝ ስለ ሞትህልኝ
በምድር ጭንቀት አለሁ
የሱስ ሆይ እጄን ያዘኝ።
ባንተ . . .።
፬፡ በየሱስ ደም ድኛለሁ
በእርሱም አጸናለሁ።
ላምላክ ምስጋና ይሁን
በልጁ ስለ አዳነኝ።
ባንተ . . .።
