Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 128 ከበደሌ ከኃጢአቴ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 128 ከበደሌ ከኃጢአቴ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ከበደሌ ከኃጢአቴ
ወዴት ልሽሽ ኦ አምላኬ?
በጣም እጨነቃለሁ
ሕግህን ሁሉ አፍርሼ
ከአንተ ርቄ ሸሽቼ
ፍርድህን እፈራለሁ።
ነፍሴንም ኀዘን ደቆሰው
ልቤንም ጸጸት ሰበረው።
ጌታዬ ሆይ ራራልኝ
ምሕረት አድርግልኝ።
፪፡ አምላክ ሆይ ቃልህ ሕይወት ነው፤
ለነፍሴ በጣም ጣፋጭ ነው፤
ልቀበለው እሻለሁ።
የሱስ ወዳለም መጥቶአል፤
ኃጢአቴን ደምስሶልኛል፤
እኔ በርሱ ድኛለሁ።
ወንበዴውን የተቀበለው፥
በገነትም ያሳረፈው፥
እኔን እንደሚቀበል፥
ቅዱስ ወንጌል ነግሮኛል።
፫፡ የሱስ ክርስቶስ የዳዊት ልጅ፥
ልቤን ከእጆቼ ጋራ
ወዳንተ አነሣለሁ።
እኔን የረከስሁ አጥራኝ፤
ከኃጢአት እድፍ አንጻኝ፤
በአንተ አምናለሁ።
እንደ ጠፋው በግ ነበርሁኝ፥
በአንተ ግን ተገኘሁኝ፤
አንተ የምትራራ
አኑረኝ ካንተ ጋራ።

Exit mobile version