Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 127 ኃጢአቴ በጣም ከብዶኛል የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 127 ኃጢአቴ በጣም ከብዶኛል የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ኃጢአቴ በጣም ከብዶኛል
ነፍሴንም ያስጨንቃል።
እንደ ሕመም ይቀፈኛል
ኃይሌን ያደነዝዛል
ዐመፃዬን ደምስስልኝ
እንዳልኰነን አድነኝ።
ፍጠርልኝ ቅዱስ አሳብ
ልቤን ወደ አንተ ሳብ።
፪፡ እንደ ቸርነትህ ማረኝ
ከበደሌም እጠበኝ።
በሂሶጵ ረጭተህ አንጻኝ
እንደ በረዶ አጥራኝ።
የማዳንን ደስታ ስጠኝ
መንፈሴን አድስልኝ።
በክንዶችህም ደግፈኝ
በመንፈስ ቅዱስ ምራኝ።

Exit mobile version