መዝሙር 121 ጽዮን ተነሺና አብሪ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ጽዮን ተነሺና አብሪ
ብርሃንሽ መጥቶአል።
አምላክ ከሰጠሽ ስጦታ
ለዓለም አካፍይ።
ያምላክ ክብር ተገልጦልሻል
አመስግኚው በደስታ
ዘምሪ ሃሌ ሉያ።
፪፡ ሀገራችን ብርሃንሽን
እንዳይጠፋ ጠብቂ፥
የጸጋ ቀን ገና ሳለሽ
ለሰላምሽ አስቢ።
ባንቺ እውነት ሰላም ይልማ፥
የአምላክ መንግሥት ይስፋ፥
ጽድቅ በአገሩ ይግዛ።
፫፡ በተራራ የተሠራ ቤት
ከሩቅ እንደሚታይ
የእውነት ፍሬ እናፍራ።
ባምላክ ቃል እንመራ
ጨው ለምድር ብርሃን ላለም
ሆነን ሕዝብን እንጥቀም
በትጋት ሳንለግም።
