Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 117 ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ታላቅ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 117 ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ታላቅ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ታላቅ ኃያል አምላክ
የንጋት መዝሙራችንን ተቀበልልን።
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ምሕረትህ የበዛ
ለሥሉስ አምላክ ይሁን ምስጋና።
፪፡ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ጻድቃን ያመስግኑህ
ዘውዳቸውን ያቅርቡ ሰግደው በፊትህ
ኪሩቤል ወ ሱራፌል ይስገዱ ለግርማህ
ለነበርክ ላለህ ደግሞም ለምትኖር።
፫፡ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ በክብር ገናና
ኃጥእ ዓይን ግርማህን ለማየት አይችልም
ኃይል ምስጋና ክብር ለአንተ ይገባል።
ፍቅር የሞላህ ግሩም ድንቅ ነህና።
፬፡ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ታላቅ ኃያል አምላክ
ፍጥረቶችህ ሁሉ ለስምህ ክብር ይስጡ።
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ኦ ሥሉስ አምላክ
ዘለዓለማዊ እግዚአብሔር።
አሜን።

Exit mobile version