Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 115 ምስጋና ክብርም ለአምላካችን የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 115 ምስጋና ክብርም ለአምላካችን የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ምስጋና ክብርም ለአምላካችን
ይገባዋል፤
ከልመናችን አብልጦ
ዘወትር ይሰጠናል።
ፍጥረት ሁሉ
በግርማው ሞልቶአል
ልንወድሰው ይገባል።
፪፡ ልባችንን መሥዋዕት
ላምላክ እናቅርብለት
በደስታና በትዕግሥት
እንታዘዝለት።
በእውነትም
እርሱን እንከተለው
ለክብሩ እንኑርለት።
፫፡ የሀገራችንን መሪዎች
አምላክ ሆይ ባርካቸው
በምክርህ ምራቸው
ከስሕተትም ጠብቃቸው።
እንደ አባት
ሕዝቦቿን እይ ኦ አምላክ
ከኃጢአትም ጠብቃቸው።

Exit mobile version