መዝሙር 112 ክርስቲያኖች በኅብረት ጌታን ስናመልክ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ክርስቲያኖች በኅብረት ጌታን ስናመልክ
እነሆ መልካም እጅግ ያማረ ነው።
የእግዚአብሔር መንፈስ በዚያ ይሰፍናል
መልካሙ መዓዛው ጠሉም ያረካል።
በዚያ የእግዚአብሔር በረከት ይፈሳል
የአማኝ ሕይወትም ይታደሳል።
ፍቅር ሰላም ደስታ ይፈልቅበታል
በልባችን ኢየሱስ ይነግሣል።
፪፡ ባምላካችን ቤት በቅዱስ መቅደሱ
የእግዚአብሔር ልጆች ልባችሁን አንሡ።
ስለ ቸርነቱ ጌታን ወድሱ
ዘምሩ ለክብሩ ስሙንም ጥሩ።
በዚያ የእግዚአብሔር . . .።
፫፡ እግዚአብሔር ታላቅ መሆኑን እንንገር
መብራታችን ይብራ ቃሉን እንመስክር።
አዲስ ቅኔ እንዘምር ይቅረብ ምስጋና
የሰላም ንጉሥ ድል ነሥቶአልና።
በዚያ የእግዚአብሔር . . .።