መዝሙር 111 ለቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ለቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ
ኃያል አምላካችን
ከመላእክቱ ጋራ
ይቅረብ ውዳሴአችን።
፪፡ ውዳሴ ስግደት ክብረት
ይገባዋልና።
ለልዑል አምላካችን
እናቅርብ ምስጋና።
፫፡ ዕልልታና ምስጋና
በደስታ አቅርቡ
በዝማሬ ውዳሴ
ወደ ቤቱ ግቡ።
፬፡ የነበርክና ያለህ
ዘለዓለም የምትኖር
አልፋና ኦሜጋ ሆይ
ላንተ ይሁን ክብር። አሜን።
