መዝሙር 103 ካምላካችን ማን ይበልጣል? የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ካምላካችን ማን ይበልጣል?
እንደርሱስ ማን ይሆናል?
ግሩም ታላቅ ኃይሉን ገልጦአል
ኦ እንዴት ያስደንቃል!
ምድርን፥ ሠራዊቷን ሁሉ
በስድስት ቀናት በቃሉ
መሠረታት በኃይሉ።
፪፡ አምላክ የፈጠረው ሁሉ፥
ግሩምና መልካም ነበር።
እባቡ ግን በተንኰሉ፥
አሳተ ሁሉን ፍጡር።
በሰይጣን ተንኰል ምክንያት፥
ካዳም በወረሰው ኃጢአት፥
ሞት ተፈርዶብን ነበር።
፫፡ ግን አምላክ ሰው ሆኖልናል፤
በሞቱ በሕይወቱም።
ታላቅ ተስፋ አግኝተናል፤
ድነናል ለዘላለም።
ፍርዳችንን ተቀበለ፤
ዕዳችንንም ከፈለ፤
አጐናጸፈን ሕይወት።
፬፡ ይህንን የሚያምን ሰው፥
በልቡም የሚቀበል፥
ይደመሰሳል አበሳው።
በየሱስ ክርስቶስ ደም ኃይል።
ከዘላለም ሞት ይድናል።
ለነፍሱም ሕይወት ያገኛል
ደስታም ይሆንለታል።
፭፡ በአብ፥ በወልድ፥ በመንፈስም
አግኝተናል ደኅንነት።
ስለ ዳንን በጌታ ደም
እናመሰግን በኅብረት።
ከሞትና ከሰይጣን ኃይል
በየሱስ ፍጹም ድነናል
ለርሱ ይሁን ምስጋና።