መዝሙር 102 ለአምላካችን በሰማይ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ለአምላካችን በሰማይ
ይገባዋል ምስጋና።
ስለ ጸጋው በእኛ ላይ
የሰጠው ለብፅዕና።
በምድር ደስታ ሰላም
ሲሰጥ ይገባናል በጣም
ፈቃዱን ልንፈጽም።
፪፡ ኦ አባት ስላንተ ምሕረት
እናመሰግናለን።
አንተ በታላቅ ቸርነት
ጸጋን አወረድህልን።
ኃያል እጅህ ሁሉን ይገዛል
ሥውር ኃጢአት ይታይሃል
ዳኝነትህ ፍጹም ነው።
፫፡ የሱስ ክርስቶስ የልዑል ልጅ
ልታድነን የመጣህ።
ከፍርድና ከሰይጣን እጅ
በሞት እኛን የዋጀህ።
በታላቅ ምሕረትህ መጠን
ከመቅሰፍት ሞት ልታድነን
በአንተ ስንማጠን።
፬፡ በመንፈስህ ልባችንን
በቃልህም አበርታን።
በልባችን መቅደስህን
ላንተ ማደሪያ ሥራ።
በመከራችን ደግፈን
አድስ ለጽድቅ ነፍሳችንን
እምነትን ጨምርለን።
