Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 99 መጣሁ ወደ መስቀልህ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ መጣሁ ወደ መስቀልህ፥
ምስኪን ነኝ ደካማም ነኝ፤
ወዳንተ እንድቀርብህ፥
ኦ መንኃኒቴ እርዳኝ።
ባንተ አምናለሁ
ብሩክ የቀራንዮ በግ፥
ተንበርክኬ በጸሎት
አድነኝ የሱስ አድነኝ።
፪፡ ያለኝን ንብረት ሁሉ፥
ሥጋዬን ቢሆን ነፍሴን
ለአንተ እሰጣለሁ፤
ለዘላለም ያንተ ነው።
ባንተ . . .።
፫፡ ያንተን ተስፋ አምናለሁ፤
እርዳኝ ስለ ሞትህልኝ።
በምድር ጭንቀት አለሁ፤
የሱስ ሆይ እጄን ያዘኝ።
ባንተ . . .።
፬፡ በየሱስ ደም ድኛለሁ፤
በእርሱም እጸናለሁ።
ላምላክ ምስጋና ይሁን፤
በልጁ ስለ አዳነኝ።
ባንተ . . .።
