Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 96 ኃጢአቴ ያሳዝነኛል የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 96 ኃጢአቴ ያሳዝነኛል የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ ኃጢአቴ ያሳዝነኛል፤
ነፍሴንም ያስጨንቃል።
እንደ ሕመም ይቀፈኛል፤
ኃይሌን ያደነዝዛል።
ዓመፃዬን ደምስስልኝ፤
እንዳልኰነን አድነኝ፤
ፍጠርልኝ ቅዱስ አሳብ፤
ልቤን ወደ አንተ ሳብ።
፪፡ እንደ ቸርነትስ ማረኝ፤
ከበደሌም እጠበኝ።
በሂሶጵ ረጭተህ አንፃኝ፤
እንደ በረዶ አጥራኝ፡
የማዳንን ደስታ ስጠኝ፤
መንፈሴን አድስልኝ፤
በክንዶችህም ደግፈኝ፤
በመንፈስ ቅዱስ ምራኝ።

Exit mobile version