Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 92 እሻለሁ ጌታ የሱስን የዘፈን ግጥሞች
፩፡ እሻለሁ ጌታ የሱስን
ይቅር የሚል በደሌን
ጋሻ ይሆንልኛል
ከኃጢአት ይጠብቀኛል።
እርሱ ሕይወት ነው ለኔ
የሱስ ነው መድኃኒቴ።
፪፡ የሱስ አንተ ነህ ተስፋዬ
አዳኜና ሕይወቴ
ሁልጊዜ ነህ አምባዬ።
አንተ እምነት ካልሰጠኸኝ
አላገኘውም በራሴ
አንተ ነህ መድኃኒቴ።
፫፡ ስለዚህ ወዳንተ የሱስ፥
ጸጋህን ተማጥኜ፥
እመጣለሁ አምኜ።
የሕይወትን ብርሃን ለኵስ
በጨለመው ልቤ
አንተ ነህ መድኃኒቴ።
