Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 91 መንግሥቱን ሕዝቡን የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 91 መንግሥቱን ሕዝቡን የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ መንግሥቱን ሕዝቡን
አምላክ ሆይ ጠብቅ፤
በረከት አውርድ በአገሩ ላይ።
በፍቅርህ ግዛን ሰላምን ስጠን፤
ጨለማውን አብራ በጽድቅ ፀሐይ።
፪፡ ጌታና ሎሌን ቤትና ጎጆ
በእጅህ ጠብቅ ከጉዳት ሁሉ።
አንተ ምራነ
በእውነተኛው መንገድ
በልባችን ፍጠር ቅዱስ ቅናት።
፫፡ የወንጌል ትምህርት ባገሩ ይስፋ፥
ዘላለማዊ ደስታን አድለን።
አርበኞች ሁነን ድል እንድነሣ፥
መንግሥትህንም ለመውረስ
አብቃን።

Exit mobile version