Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 9 ኦ ግሩም ጊዜ፥ ኦ ብሩክ ሰዓት የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ኦ ግሩም ጊዜ፥ ኦ ብሩክ ሰዓት፥
ለቅዱሳን ለነቢያት፤
የታየው ቀን መጣልን።
እንደ አምላካችን ሥምረት፥
ዘላለማዊ ምሕረት፥
ለእኛ ወረደልን።
የሱስ ክርስቶስ ሰው ሆነልን፤
እናመስግን በአንድነት፤
እንወድሰው በእምነት።
፪፡ እንደ አብ ፍጹም አምላክ ነው፤
እንደኛም ሆነ ፍጹም ሰው
ወዳምላክ ሊያቀርበን።
የጠፉትን ይፈልጋል፥
ሰላሙንም ይሰጠናል፥
መድኃኒትም ሆነልን።
ከኵነኔ እንዲአድነን፥
አብ ፈቃዱን እንዲፈጽም፥
ወልድን ላከ ወደ ዓለም።
፫፡ በመከራችን አልቅሶ፥
ጭንቃችንን አስታውሶ፥
በመንፈሱ ሊመራን፥
የአብንም ፈቃድ ሊገልጥል፥
ከጭንቀትም እንድናመልጥ፥
ሙሉ ረደኤት ሆነልን።
እርሱ ለኛ ሕይወት ሊሆን፥
የሞት ፃዕርን ታገሠልን፤
የጽድቅን በር ከፈተልን።
፬፡ ጨለማው ዘመን አልፎአል፤
የጽድቅ ፀሐይም ወጥቶአል፤
ብርሃን እንዲሆንልን።
የሱስን እንከተለው፤
በእውነት እረኛችን ነው፤
ራሱን የለወጠልን።
በርሱ ፍጹም ተስፋ አለን፤
እንዲሰጠን ፍሩም ብፅዕና፤
ለእርሱ ይሁን ምስጋና።