Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 89 ምስጋና ክብርም ለአምላካችን የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ምስጋና ክብርም ለአምላካችን
ይገባዋል፤
ከልመናችን አብልጦ
ዞትር ይሰጠናል።
ፍጥረት ሁሉ
በግርማው ሞልቶአል፤
ልንወድሰው ይገባል።
፪፡ ልባችንን መሥዋዕት
ላምላክ እናቅርብለት፤
በደስታና በትዕግሥት
እንታዘዝለት።
በእውነትም
እርሱን እንከተለው፤
ለክብሩ እንኑርለት።
፫፡ የኢትዮጵያን ገዦች
አምላክ ሆይ ባርካቸው፤
በምክርህ ምራቸው
ከስሕተትም ጠብቃቸው።
እንደ አባት
ሕዝቦቿን እይ ኦ አምላክ፤
ከኃጢአትም ጠብቃቸው።
