Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 88 ቸር አምላክ ሆይ በመቅደስህ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ቸር አምላክ ሆይ በመቅደስህ
መሰብሰብ ደስ ያሰኛል።
በዚህ ይገለጣል ክብርህ
ሕያው ቃልህ ይሰማል።
አንተን እያሰበ ልቤ
ያቀርብልሃል ውዳሴ
ደስታም ይሞላበታል።
፪፡ ከዓለም ደስታ ይልቅ
አንተን ማግኘት ይበልጣል።
ካንተ ካምላኩ የሚርቅ
ከሰላምህ ይለያል።
የሕሊና ዕረፍት የለውም
ሕይወትንም አያገኝም
ለዘላለም ይጠፋል።
፫፡ ታላቅ በረከትን ሰጥተህ
ወገኖችህን አጽናና።
ልመናቸውንም ሰምተህ
ሕይወታቸውን አርካ።
ቤተ ክርስቲያንህን ቀድስ
ባንተ እንድትመላለስ
ኃይልህንም ሙላባት።
፬፡ መንፈስህን ላለም አውርድ
በአንተ እንዲጸና።
ሁሉን ምራው በቅን በመንገድ
ጠብቀው ከፈተና።
ቅዱስ ቃልህን ለመስማት
ጠንካራ የእምነት ትጋት
በሁሉ ሰው አሳድር።
፭፡ ኦ አብ፥ ላንተ ስብሐት ይሁን፥
ኦ ወልድ እናመስግንህ።
ኦ መንፈስ ቅዱስ ቀድሰን፥
አትለየን በፍቅርህ።
ስንሄድም ከዚህ ዓለም
በመቅደስህ ለዘላለም፥
አድለን ብጽዕና።
