Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 82 ቅዱሳን በጌታችን ፊት የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 82 ቅዱሳን በጌታችን ፊት የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ ቅዱሳን በጌታችን ፊት
ይቆማሉ፥
ይሰግዳሉ በሃይማኖት፥
በእርሱ ታምነው።
፪፡ ነጭ ልብስን ለብሰው
ዘንባባን በእጃቸው
ይዘው፥ ለርሱ ምስጋናን
ሰጡ እንዲህ ብለው
፫፡ ገናናነት በዙፋን ላይ
ለሚቀመጥ፥
ለአምላካችን በሰማይ፥
ክብር ምስገና እንስጥ።
፬፡ መላእክት በዙሪያው ቁመው
ሰገዱለት፥
ሽማግሎችም በዚያው
ምስጋና ሠውለት።
፭፡ በግንባራቸው ወደቁ
ሰገዱለት፥
ለልዑል አምላክ ለበጉ
ይሁንለት ስብሐት።
፮፡ ግርማና ክብር ጥበብም
ለርሱ ይሁን፥
ምስጋና ኃይል ችሎትም
ይገባዋል አሜን።

Exit mobile version