Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 75 ኦ መንፈስ ቅዱስ ና ወደኔ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 75 ኦ መንፈስ ቅዱስ ና ወደኔ የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ ኦ መንፈስ ቅዱስ ና ወደኔ፤
ልቤንም ክፈት ለአንተ።
በእውነቱ የምትመራ፥
የጨለመ ልቤን አብራ።
፪፡ የኃጢአት ጸጸት ሲሞርደኝ፥
ፍርሃት፥ ጭንቀት ሲያውከኝ፥
ጸንቼ እንድገኝ በቃልህ፥
አትለየኝ በምሕረትህ።
፫፡ ከክፉ ምኞት ነፍሴን አንጻ፥
አኑረኝ በቅድስና።
ጥርጥርም እንዳይገባብኝ፥
በቸርነትህ ጠብቀኝ።
፬፡ ጠማማ ፈቃዴን አቅና፤
ሰላምህ ይንገሥ በልቤ።
በዚች ዓለም ለአምላክ ክብር፥
ለሰውም ጥቅም እርዳኝ ልኑር።

Exit mobile version