Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 73 የየሱስ ክርስቶስን ዕርገት የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 73 የየሱስ ክርስቶስን ዕርገት የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ የየሱስ ክርስቶስን ዕርገት
አያለሁ በሃይማኖት።
ኀዘን ቢበዛ ጭንቀትም፥
ለጌታ ከኖርሁለት፥
ተማጥኜ በርሱ ሥቃይ፥
እደርሳለሁ ወደ ሰማይ።
፪፡ ከኃጢአቴ ተፈትቼ
ሆኛለሁ ለጌታዬ፤
ያን ክቡር አገር አይቼ
ይኼ ነው ዓላማዬ።
ልኖር ከብፁዓን ጋራ፥
ጌታ ባዘጋጀው ስፍራ።
፫፡ ባዲሲቱ የሩሳለም
መከራ፥ ጭንቀት የለም።
እዚያ ነው ያለው መዝገቤ፤
የሚታሰብ በልቤ።
ከየሱስ አለኝ አንድነት፤
ያለርሱ የለኝም ሕይወት።
፬፡ ያረገው ወደ ላይ ከእኛ፥
ይመለሳል ዳግመኛ።
እንዳይመጣ ሳናስበው፥
ተግተን እንጠብቀው።
እምነታችን እንዳይናጋ፥
ዞትር በጸሎት እንትጋ።
፭፡ በቅዱስ ስምህ ያመነ፥
አንተን የተማጠነ፥
መንግሥትህን እንደሚወርስ፥
ተስፋ ሰጠህ ኦ የሱስ።
ብፅዕና ትሰጠዋለህ፤
በክብርም ታኖረዋለህ።

Exit mobile version