Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 64 ክርስቶስ ዛሬ ተነስቶአል የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ክርስቶስ ዛሬ ተነስቶአል፥
ሃሌ ሉያ።
ቅዱስ ቀናችን ነግቶአል፥
ሃሌ ሉያ።
በመስቀሉ የሞተልን ሃሌ ሉያ።
ዕዳችንን ሊያስወግድልን
ሃሌ ሉያ።
፪፡ ለክርስቶስ ንጉሠ ስብሐት
ሃሌ ሉያ።
ውዳሴን እናቅርብለት
ሃሌ ሉያ።
በመቃብር ለተኛ ሃሌ ሉያ።
ሕይወት ይሰጥ ዘንድ ለኃጢአተኛ
ሃሌ ሉያ።
፫፡ በሥቃይ አዳነን
ሃሌ ሉያ።
መድኃኒትም ሆነልን
ሃሌ ሉያ።
አሁን በሰማይ ነግሦአል ሃሌ ሉያ።
መላእክትም በዙሪያው ቁመዋል
ሃሌ ሉያ።
፬፡ ምስጋና ለአምላካችን
ሃሌ ሉያ።
እናቅርብለት ሁላችን
ሃሌ ሉያ።
ዓለም ሙሉ ይቀደስ ሃሌ ሉያ።
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ
ሃሌ ሉያ።
