Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 61 የደስታ ዘመን ሆኖአል የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 61 የደስታ ዘመን ሆኖአል የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ የደስታ ዘመን ሆኖአል፥
ክርስቶስ ሞትን ድል ነሥቶአል።
ሲነሣም ከመቃብሩ
ተገለጠ ታላቅ ክብሩ።
፪፡ ከኩነኔ ሊያድነን፥
ተነሣ በሦስተኛው ቀን።
እንዲያርግ ተነሥቶ ከሞት፥
ተነግሮአል በነቢያት።
፫፡ ቢጠብቁም መቃብሩን
ተነሣ ጥሶ ድንጋዩን።
የሕይወት ንጉሥም ቢሞት
አልቀረም በሲኦል ግዞት።
፬፡ ሲኦል አሁን ተሸነፈ
የስቃይ ዘመን አለፈ።
ሃሌ ሉያ ተነሥቶአል፤
ጌታችን እንደ ተስፋው ቃል።
፭፡ ከሞት ሥልጣን ያወጣኸን፤
ኦ የሱስ ክርስቶስ ተመስገን።
ሙታን በሚነሡበት ቀን፥
የሕይወት ትንሣኤ ስጠን።

Exit mobile version