Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 56 የሞተልኝ ጌታዬን የሱስን ሳስበው የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 56 የሞተልኝ ጌታዬን የሱስን ሳስበው የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ የሞተልኝ ጌታዬን የሱስን ሳስበው
በጣም ያስደንቀኛል
ምን ዓይነት ፍቅር ነው?
ምን ዓይነት ፍቅር ነው?
ምን ዓይነት ፍቅር ነው?
በቀናንዮ ኮረብታ ለኔ የገለጽከው።
ምን ዓይነት ፍቅር ነው?
ምን ዓይነት ፍቅር ነው?
በቀናንዮ ኮረብታ ለኔ የገለጽከው።
፪፡ ስለ ሞተልኝ የሱስ
ለመናገር ፍቅሩን፥
ይቸግራል ለምላስ
አልችለውም ፍጹም።
ምን ዓይነት . . .።
፫፡ በመስቀል ተቸንክረው
እጆችና እግሮችህ፥
ተቀጣህ ስለኔ ኃጢአት
መርገምን ተሸክመህ።
ምን ዓይነት . . .።
፬፡ ኃጢአት ሳይኖርብህ
ቅዱስ የኔ ጌታ፥
ስለ ኃጢአቴ ነው
የሞትክ በጐልጐታ።
ምን ዓይነት . . .።
፭፡ ጌታ የሱስ ክርስቶስ
ያለም ሁሉ አዳኝ፥
አስደናቂ ፍቅርህን
እንዳስበው እርዳኝ።
ምን ዓይነት . . .።

Exit mobile version