Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 52 ቸሩ መድኃኒቴ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 52 ቸሩ መድኃኒቴ የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ ቸሩ መድኃኒቴ
የመጣህ በፍቅርህ፥
ወደ ዓለም ውርደት
ከጥንታዊ ክብርህ።
፪፡ ሕይወቴን ለማዳን
ተሸክመህ ቅጣት፤
ፍቅርህ አደረሰህ
ለሥቃይና ሞት።
፫፡ አቤቱ ፍቅርህን
ግለጣው በላዬ፤
ብርሃንህን ስጠኝ
በጨለመ ልቤ።
፬፡ በጨለማ ዓለም
ለታሰረ ለፍሱ፥
የጸጋን አርነት
ግለጥለት ለርሱ።

Exit mobile version