Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 41 ፍርዳችንን የወሰድኸው የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ፍርዳችንን የወሰድኸው
መስቀልን የተሸከምኸው።
ከሞትም ኃይል ያወጣኸን
ኦ የሱስ ክርስቶስ ተመስገን።
ኦ የሞትህልን አድነን።
ስማልን ጸሎታችንን
፪፡ ታላቅ ሥራህ ተፈጸመ
ፍርድ ምሕረቱን አተመ።
የፍርድ አምላክ ለኃጢአት
ከሰጠ በቂውን ቅጣት።
መሐሪ አምላክ ልጆቹ
አደረገን በምሕረቱ።
፫፡ እኛ ፍጹም ደካሞች ነን
ጌታ የሱስ ሆይ አበርታን።
በምሕረት እጅህ ደግፈን
በቅዱስ መንፈስህ እርዳን።
ያምላክ ልጆች ያደረግኸን
የሱስ ክርስቶስ ሆይ ተመስገን።
፬፡ አትራቅብን የሱስ ሆይ
ሁልግዜ ከኛ ዘንድ ቆይ።
በፈተና አበርትተህ
በትግልም አጠንክረህ።
በሕይወትም በሞትም ጻር
በደምህ ኃይል ሁን ከኛ ጋር።