Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 4 መንገድ አብጅ ለጌታ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 4 መንገድ አብጅ ለጌታ የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ መንገድ አብጅ ለጌታ
ጠማማውም ይቅና።
ይመጣል ወደ እኛ
የእስራኤል ተስፋ።
የጽድቅም ገዥ ይሆናል
ሥልጣኑን ይጨብጣል።
ከአብ የመጣልን
እርሱን እናመስግን።
፪፡ ነዋሪ ንጉሣችን
ወደኛ መጣልን።
ተስፋው ተፈጸመልን
ደኅንነት አገኘን።
ቃሉ እውነት ነውና
ዘምሩ ሆሣዕና።
ከአብ . . .።
፫፡ የልብህን በር ክፈት
የክብር ንጉሥ ይግባ።
ይሰጣል ደኅንነት
የሱስ ያለም ተስፋ።
በምድር ዙሪያ ሁሉ
ሕዝቦች እንዲህ ዘምሩ።
ከአብ . . .።

Exit mobile version