Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 39 አዳኜ ደሙ ፈሰሰ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 39 አዳኜ ደሙ ፈሰሰ የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ አዳኜ ደሙ ፈሰሰ
መድኅኔ ሞተልኝ።
እርሱ ራሱን አዋረደ
እኔን ሊያድነኝ።
በክርስቶስ በክርስቶስ
ብርሃንን አገኘሁ
የልቤ ሸክም ተወገደልኝ።
በእርሱ ነው እምነትን ያገኘሁ።
በዚህ ደስታዬን እገልጻለሁ።
፪፡ የተሠቃየው መድኅኔ
ስለኔ ኃጢአት ነው።
ሕይወት ሊሆንልኝ ለኔ
አምላክ ልጁን ሠዋው።
በክርስቶስ . . .።
፫፡ ያምላክ ልጅ በታላቅ ፍቅሩ
ሕይወቱን ሠዋልኝ።
የርሱ ወገን ሊያደርገኝ
አፈሰሰ ደሙን።
በክርስቶስ . . .።
፬፡ እንባዬ ሲፈስ በኀዘን
ዕዳዬን አይከፍልም።
ግን ኢየሱስን በማመን
እድናለሁ ፍጹም።
በክርስቶስ . . .።

Exit mobile version