Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 38 የሱስ ሆይ፥ በመስቀል ላይ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ የሱስ ሆይ፥ በመስቀል ላይ
በመሠቃየትህ፥
የዘላለም ነፃነት
ለሁሉ አስገኘህ።
መስቀልህ፥ መስቅልህ፥
ለሁሉ ኃይል ሆነ።
ነፍሴ ምሕረት ካገኘች፥
በሰላም ታርፋለች።
፪፡ በመስቀልህ አጠገብ
ነፍሴ ስትጨነቅ፥
ግሩም የደኅንነት ብርሃን
በልቤ ይፈንጠቅ።
መስቀልህ . . .።
፫፡ ኦ የሱስ የአምላክ በግ፥
ሰላምህን ስጠኝ።
ከዚህ ዓለም መከራ
ሁልጊዜ ታደገኝ።
መስቀልህ . . .።
