Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 343 የየሱስን መልካሙን ድምጽ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 343 የየሱስን መልካሙን ድምጽ የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡  የየሱስን መልካሙን ድምጽ
ሰምተሃል ወይ ወንድሜ ሆይ?
ሁሉን ትተህ ተከተለኝ
አገልጋዬም ሁነኝ ይልሃል።
አምላኬ ሆይ፥ ልከተልህ
አምላኬ ሆይ ልከተልህ
አምላኬ ሆይ ወድጃለሁ
ልከተለህ መላውን ዘመኔ።
፪፡  ትችላለህ ወይ ልትጠጣ
የጌቴሴማኒን ጽዋ?
ለጸሎት ትነቃለህ ወይ
አባትህን ልትለምነው?
አምላኬ ሆይ . . .።
፫፡  የወጣትነትህን ኃይል
ልትሰጥ ትወዳለህ ወይ?
ትሰጣለህ ወይ ሕይወትህን
ለጌታ ለየሱስ  ላምላክህ?
አምላኬ ሆይ . . .።
፬፡  እንግዲህ ወንድሜ ሆይ ና
እምነትህን የጠበቅኸው
አምላክህ ወዶአልና
የሕይወትን አክሊል ሊሰጥህ።
አምላኬ ሆይ . . .።

Exit mobile version