Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 342 ፍቅር ታጋሽ ናት የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ፍቅር ታጋሽ ናት
ያለ ምቀኝነት
ፍቅር አትመካም
ፍቅር አታኮርፍም
ፍቅርም ፊትዋን
አታጠቁርም
ፍቅርም ገንዘብዋን
ከቶ አትፈልግም።
፪፡ ቍጣ አታውቅም
ክፉ አታስብም።
ፍቅር ከእውነት ጋር
ዞትር ደስ ይላታል
በማንም ኃጢአት
ከቶ ደስ አይላትም።
ሁሉን ትታገሳለች
በተስፋ በእምነት።
፫፡ የክርስቶስ ፍቅር
ከቶ አትወድም።
ዳሩ ግን ትንቢቶች
መልሰው ያልፋሉ።
በልሳን ቋንቋም
መናገር ይቀራል።
ማስተዋል የተባለ
በሙሉ ይጠፋል
፬፡ ከእውቀት ከፍለን
እናውቃለንና።
እንናገራለንና፤
ፍጹም ግን የሚሆን
በደረሰ ጊዜ
ከፍለን ያወቅነው ቀርቶ
ፍቅር ትኖራለች።
